ኢትዮጵያ በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ አዘጋጇ ኢትዮጵያ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፏን አረጋገጠች።
በምድብ አንድ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ሶማሊያ ሩዋንዳን 3 ለ 0፣ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ውጤቶቹን ተከትሎ ኬንያ በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ሶማሊያ በምድቧ ያደረገችውን አራት ጨዋታዎች አጠናቃ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።
ደቡብ ሱዳን በአንድ አራተኛ እና ሩዋንዳ ያለ ምንም ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በሰባት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያላትን ኬንያን በግብ ክፍያ በልጣ አንድ ጨዋታ እየቀራት ለግማሽ ፍጻሜ አልፋለች።
ኬንያም ለግማሽ ፍጻሜው ማለፏን አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈችው ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሩዋንዳ በነጥብ የማይደርሱባት በመሆኑ ነው።
አዘጋጇ ኢትዮጵያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋን ከነገ በስቲያ ከኬንያ ጋር ታደርጋለች።
ኢትዮጵያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋን ከነገ በስቲያ ከኬንያ ጋር ታደርጋለች።
በምድብ ሁለት ታንዛንያ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፏ ይታወቃል።