ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ መሰሉ አበራ እና ታደለች አብርሃም ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ18 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ዛሬ በተደረገ የስምንተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም