ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥራለች።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ24 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

በሊጉ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ጎሎች ብዛት  
ወደ 16 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቷን አጠናክራለች።

በአሁኑ ሰዓት ሸገር ከተማ ከሃዋሳ ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም