ቀጥታ፡

የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፡- የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብለን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ አስጎብኝተናቸዋል ብለዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ ከተማ አዲስ አበባ ያማረ ቆይታ እንዲኖራቸውም ተመኝተዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ትናንት ማታ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም