ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ከቀኑ 7 ሰዓት ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ21 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ካሸነፈ የሊጉን መሪነት ያጠናክራል። 

ሲዳማ ቡና በሰባተኛ ሳምንት በድሬዳዋ ከተማ ካጋጠመው ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ሸገር ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ አምስተኛ፣ ሃዋሳ ከተማ በ15 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ወቅታዊ ብቃታቸው በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሁለት ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል ።

የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሕዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም