ቀጥታ፡

በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ዛሬ 10ኛ ቀኑን ይዟል። 

በምድብ አንድ ሩዋንዳ ከሶማሊያ ከቀኑ 7 ሰዓት በአበበ በቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

በምድቧ ያደረጋቻቸውን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈችው ሩዋንዳ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በሶስቱም ጨዋታዎቿ አቻ የወጣችው ሶማሊያ በበኩሏ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። 

በዚሁ ምድብ ከቀኑ 10 ሰዓት ኬንያ ከደቡብ ሱዳን በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ከሁለት ጨዋታዎች አራት  ነጥብ ያገኘችው ኬንያ በአራት ነጥብ ሁለተኛ፣ ደቡብ ሱዳን በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ምድቡን በሰባት ነጥብ የምትመራው ኢትዮጵያ በአራተኛ የምድብ ጨዋታዎች አራፊ ሀገር ናት። 

በተያያዘም በምድብ ሁለት ታንዛንያ ከብሩንዲ ከቀኑ 10 ሰዓት በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይጫወታሉ። 

ታንዛንያ ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ እየመራች ነው። ከሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያገኘችው ብሩንዲ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። ታንዛንያ ከድቡ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ የተሻለ እድል አላት። 

ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጅቡቲ ከሱዳን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ። 

በምድባቸው በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎችን ሽንፈት ያስተናገዱት ጅቡቲ እና ሱዳን ባለባቸው የግብ እዳ ተበላልጠው አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ስድስት ነጥብ ይዛ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ዩጋንዳ በዚህኛው ዙር አራፊ ሀገር ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም