በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ12ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በሳንሲሮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክርስቲያን ፑሊሲች በ54ኛው ደቂቃ የማሸነፊያው ጎል አስቆጥሯል።
ኢንተር ሚላን በ74ኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሃካን ቻላንሆግሉ አልተጠቀመበትም።
ኢንተር በጨዋታው ያገኛቸውን የግብ እድሎች መጠቀም አለመቻሉ ዋጋ አስከፍሎታል።
ውጤቱን ተከትሎ ኤሲ ሚላን በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
ኢንተር ሚላን በ24 ነጥብ ከሁለተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል። የሊጉ መሪ የመሆን እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በተያያዘም ክሬሞኔንሴን 3 ለ 1 ያሸነፈው ሮማ በ27 ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።