የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 14/2018 (ኢዜአ)፦ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ገልጸዋል።
ይህ ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት አጋርነትን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ሲሆን፣ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር እድሎችን ለመዳሰስም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።