አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ለኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ለኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ በጁቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።
ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)ን በይፋ መቀበላቸው እና አምባሳደሩ የኢጋድ አምባሳደሮች ኮሚቴ አባል መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዋና ፀሐፊው ከአምባሳደር ለገሰ ጋር በቁልፍ ቀጣናዊና ተቋማዊ የቅድሚያ ትኩረት መስኮች ላይ መወያየታቸውንም ገልጸዋል።
የኢጋድ አምባሳደሮች ኮሚቴ የኢጋድ እና ኢትዮጵያን የጋራ አጀንዳ ለማራመድ ቁልፍ ሚና የሚወጣ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ማዕቀፍ መሆኑንም ድርጅቱ አስታውቋል።