ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቡድን 20 ጉባኤ ያደረኳቸውን ሁለትዮሽ ውይይቶቼ የመጨረሻ የሆነውን ውይይት ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ አተኩረን አከናውነናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም