ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በነበረን ውይይት በኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር ውይይት አድርገን ነበር ብለዋል።


 

ከኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ቁልፍ መዳረሻዎች አንዷ የሆነችው ኔዘርላንድ ኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ጉልህ አቅም አላት ሲሉም ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ትብብርን አስመልክቶም እድሎቻችንን ለመመልከትና የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በጉብኝቶች እና የልውውጥ መርሃ ግብሮች እንድንከውን በውይይቱ ሀሳብ አንስቻለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም