COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ብራዚል የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከብራዚልፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይቱ ፥ በኢኮኖሚ እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ አተኩረን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የምናጠናክርባቸውን እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ እንደነበር ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፥ ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ ብለዋል።
የአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደናል ነው ያሉት።