ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካፍ ፕሬዝደንት ከዶክተር ፓትሪስ ሞትሲፒ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካፍ ፕሬዝደንት ከዶክተር ፓትሪስ ሞትሲፒ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካፍ ፕሬዝደንት ከዶክተር ፓትሪስ ሞትሲፒ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በአፍሪካ እግር ኳስ እና ኢትዮጵያ በእድገቱ ስለሚኖራት ሚና ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
እንዲሁም ለወጣቶች እድገት፣የስፖርት መሠረተ ልማት ብሎም የአፍሪካን እግርኳስ በአለም መድረክ ለማላቅ ከካፍ ጋር ኢትዮጵያ ስለሚኖራት ትብብር መወያየታቸውን ነው የገለጹት።