ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የባለብዙ ወገን ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማት ያሉ የጋራ አለምአቀፋዊ ትኩረት በሚጠናከርበት መንገድ ላይ ያጠነጠነ እንደነበር ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሊደረግ ስለሚችለው ድጋፍም ከዋና ጸሃፊው ጋር መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም