ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን በተካሄደው Compact with Africa (CwA) መርሃ ግብር ላይ ተካፈሉ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን በተካሄደው Compact with Africa (CwA) መርሃ ግብር ላይ ተካፍለዋል።

መርሃ ግብሩ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የወደፊት ትልሙን መመልከት ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ሥራዎችን፣ እንደ ገበያን ክፍት የማድረግ ተግባራት፣ የቁጥጥር ማህቀፎች የማጠናከር ሥራዎች፣ የካፒታል ገበያዎችን የማበርታት እንቅስቃሴዎች ያሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎችን አንስተው የረጅም ጊዜ የግል ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ እንዳስቻሉ ማውሳታቸውንም ገልጿል


 

መርሃግብሩ Compact with Africa 2.0 የአፍሪካን ብሎም የሰፊውን አለም የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ርዕይ ሊይዝ እንደሚገባ ጥሪ በማስተላለፍ ተጠናቅቋል ነው ያለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም