አትሌት መልክናት ውዱ የ25ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት መልክናት ውዱ የ25ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ አትሌት መልክናት ውዱ የ25ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪ.ሜትር የጎዳና ውድድር አሸናፊ ሆናለች::
የሩጫ ውድድሩ "ሀገር በ10 ኪሎ ሜትር ትደምቃለች "በሚል መሪ ቃል 55 ሺህ ህዝብ የሚሳተፍበት የጎዳና ላይ ውድድር መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጓል።
ታላቁ ሩጫ ከስፖርቱ ባለፈ የሀገር ገጽታ በመገንባት እና ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል።