ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቡድን 20 መሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን ከህንድ፣ ቬይትናም፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቡድን ሃያ መሪዎች ስብሰባ ፍሬያማ እና ትርጉም ያላቸው ተጨማሪ ውይይቶችን ከህንድ፣ ቬይትናም፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር አካሂደናል ብለዋል።