ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር መልካም ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በሁለቱም ሀገሮቻችን ቅድሚያ በምንሰጠው በንግድ እና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ባተኮረ የግብርና ማዘመን ሥራ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተነጋግረናል ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።