ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት አጄይ ባንጋ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት አጄይ ባንጋ ጋር በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው ብለዋል።


 

በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተናል ሲሉም ገልጸዋል።

ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ ነበር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም