ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተገናኝተን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ጠንካራውን እና ለረጅም ዘመናት የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደፊት ማራመድ በማስፈለጉ ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።