ማንችስተር ሲቲ ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃርቪ ባርንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።
ሩበን ዲያዝ ለማንችስተር ሲቲ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ22 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ሰማያዊዎቹ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥለዋል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን ያሳካው ኒውካስትል ዩናይትድ በ15 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።