ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ ትብብር፣ የጋራ ትኩረት በሚሹ የባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሀገራቱን ትብብር በሚያጠናክሩ እና ዘላቂ እድገትን በሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ መነጋገራቸውንም አመልክተዋል።