ባህር ዳር ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወንድወሰን በለጠ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ11 ነጥብ ከአምስተኛ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።
ጨዋታውን ተከትሎ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።