ቀጥታ፡

ሊቨርፑል በኖቲንግሃም ፎረስት ተሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው በኖቲንግሃም ፎረስት የ3 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
 
ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሙሪሎ፣ ኒኮሎ ሳቮና እና ሞርጋን ጊብስ-ዋይት ለኖቲቲንግሃም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ከስምንተኛ ወደ 11ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።


 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች በአራቱ ሽንፈት አስተናግዷል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኖቲንግሃም ፎረስት በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ19ኛ ወደ 16ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።


 

በሌሎች ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ዎልቭስን 2 ለ 0፣ ብራይተን ብሬንትፎርድን 2 ለ 1 እና ፉልሃም ሰንደርላንድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ቦርንማውዝ እና ዌስትሃም ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም