ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ) ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ውይይቱ በቁልፍ የጋራ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል።
ትስስራችንን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመፈለግ ያለንን ፍላጎት ገልጸናል ብለዋል፡፡