ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ) ፦  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤   የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተከናወኑ ባሉ ትብብሮች መጠናከሩን ገልጸዋል። 


 

በዚህ ረገድም ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ትብብሮቹ ስላሉበት ደረጃ መወያየታቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም