ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ) ፦  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ጋር ተወያይተዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሁለትዮሽ ውይይቱ የኢትዮ-አውሮፓ ኅብረት ግንኙነት የማላቅ አላማ እንዳለው ገልጸዋል። 


 

በውይይቱ በተለያዩ ዘርፎች ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር አቋማችንን እንደገና አጽንተናል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም