ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት፣በትምህርት ፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እንዲሁም በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል ብለዋል። 


 

ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም