ቀጥታ፡

ቼልሲ በርንሌይን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቼልሲ በርንሌይን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በተርፍ ሙር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፔድሮ ኔቶ እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።


 

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ23 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው በርንሌይ በ10 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም