ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ፕሬዝዳንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) ፕሬዝዳንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን ከአይ.ኤም.ኤፍ ፕሬዝዳንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ፣ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲሁም ዘላቂ እና አካታች እድገትን ለመደገፍ ትብብርን ለማጠናከር ያሉ እድሎች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።


 

ለአይ.ኤም.ኤፍ የዘለቀ ግንኙነት ምስጋናቸውን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ትኩረቶቻችንን ለመፈፀም መነሳታችንን እገልጻለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም