ቀጥታ፡

ምድረገነት ሽሬ እና  መቻል ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ምድረገነት ሽሬ እና መቻል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳንኤል ዳርጌ እና አቤል ማሙሽ ለምድረገነት ሽሬ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በረከት ደስታ እና አብዱልከሪም ወርቁ ለመቻል ጎሎቹን ከመረብ ላይ ያሳረፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ውጤቱን ተከትሎ ምድረገነት ሽሬ በስድስት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።

መቻል በ12 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና የመረከብ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም