በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በርንሌይ ከቼልሲ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ - ኢዜአ አማርኛ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በርንሌይ ከቼልሲ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ በ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይመለሳል።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኒውካስትል ዩናይትድ በ12 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ ያደርጋል።
በአንጻሩ ኒውካስትል ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ነው።
ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በርንሌይ ከቼልሲ በተርፍ ሙር ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በርንሌይ በ10 ነጥብ 17ኛ፣ ቼልሲ በ20 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ጨዋታው በርንሌይ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ቼልሲ በድል ጉዞው ለመቆየት የሚያደርጉት ነው።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት ምሽት 12 ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ኖቲንግሃም ፎረስት በዘጠኝ ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቀያዮቹ ወደ ዋንጫው ፉክክር ለመመለስ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል። ኖቲንግሃም ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና እንዲወጣ ያስችለዋል።
በሌሎች መርሃ ግብሮች ቦርንማውዝ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ዎልቭስ ከክሪስታል ፓላስ፣ ብራይተን ከብሬንትፎርድ እና ፉልሃም ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።