ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ የአዘጋጇን ሀገር ደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል።


 

ታሪካዊው የጂ-20 ጉባኤ በአፍሪካ ምድር እንደመሰናዳቱ በተለያዩ ጉዳዮች እንዲሁም በጉባኤው የአፍሪካ የወል ድምጽ እና የጋራ ፍላጎት የሚቀርብበትን ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም