ቀጥታ፡

ታንዛንያ ዩጋንዳን በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈች የመጀመሪያ ሀገር ሆነች

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት ጨዋታ ታንዛንያ ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ማምሻውን በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዲስማስ አትሃናስ እና ሶአን አዳም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኢስማኤል ፋሃድ ለዩጋንዳ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ታንዛንያ በዘጠኝ ነጥብ አንድ ጨዋታ እየቀራት ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች።

በምድቡ የመጀመሪያ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ዩጋንዳ በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ጅቡቲን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም