ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ ዳርዛ በአራተኛ ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ወላይታ ድቻ መሪ ሆኗል። 

ናትናኤል ዳንኤል በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ አድርጓል። 

ወላይታ ድቻ በሁለት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም። 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰባት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም