ቀጥታ፡

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ አንድ ጨዋታ አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ሶስት አቻ ተለያይታለች።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳዊት ካሳው በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። አቤኔዘር አለማየሁ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኑርአብዲራሺድ ለሶማሊያ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቢላል ዩሱፍ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሰባት ነጥብ የምድብ መሪነቷን አጠናክራለች።

ሶማሊያ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

የኢትዮጵያው አጥቂ ዳዊት ካሳው በውድድሩ ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ወደ ስድስት ከፍ በማድረግ ተመሳሳይ የግብ መጠን ካስቆጠረው ከታንዛንያው ሉክማን አሊ ጋር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ እየመራ ነው።

በምድብ አንድ ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ኬንያ ሩዋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም