ቀጥታ፡

በተጠባቂው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 2 አሸንፏል። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አማኑኤል ኤርቦ እና ብሩክ ሙሉ ጌታ በጨዋታ ዩጋንዳዊው አለን ካይዋ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በፍቃዱ አለማየሁ እና ተመስገን ታደሰ ለኢትዮጵያ ቡና ጎሎቹንን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በስምንት ነጥብ ደረጃውን ወደ ዘጠነኛ ከፍ አድርጓል። 

በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም