በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኬንያ ሩዋንዳን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኬንያ ሩዋንዳን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘች
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ አንድ ጨዋታ ኬንያ ሩዋንዳን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኒኮላስ ኦቾላ እና ትሬቨር ናሳሲሮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ንሺሚዪማና ኦሊቨር ለሩዋንዳ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ኬንያ በአራት ነጥብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ሩዋንዳ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።
በምድብ አንድ አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታዋን ታደርጋለች።