በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ በተደረገው ጨዋታ መሰረት ማቴዎስ እና ድንቅነሽ በቀለ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አስራት ዓለሙ ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርባምንጭ ከተማ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በሶስት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃ ይዟል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።