ሃዋሳ ከተማ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ሃዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ ታደለ በ16ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ሃዋሳ ከተማ በ13 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ እስከ አሁን ድል ያላስመዘገበው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።