ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ በኬንያ ክዋሌ እየተካሄደ የሚገኘው ዓመታዊው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

በሴቶች የጎዳና ላይ ውድድር  ፅጌ ካህሳይ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሩ ላይ የአልጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሪሺየስ እና ሩዋንዳ ብስክሌተኞች ተሳትፈዋል።

ፅጌ ትናንት በግል የሰዓት ሙከራ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ የሚታወስ ነው።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘችውን የወርቅ ሜዳሊያ ወደ ሁለት ከፍ ማድረጓን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ29 ሀገራት የተወጣጡ ብስክሌተኞች በውድድሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል።

ሻምፒዮናው እስከ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም