በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ሃዋሳ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ በተደረገው ጨዋታ የምስራች ላቀው ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ቻይና ግዛቸው ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ቃልኪዳን ጌታሁን ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።