ቀጥታ፡

​​​​​​​ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንድን ነው?

• የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ነው።

• በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤

👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፤

👉 የጡንቻ እና ጀርባ ህመም፤

👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፤

👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ፤

👉 ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከሁለት እስከ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ።

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

• በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፤

• በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች፣ እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚኖር ንክኪ፤

• በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም