ቀጥታ፡

ይርጋጨፌ ቡና በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይርጋጨፌ ቡና ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ በሬዱ በቀለ በስምንተኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

 ሸገር ከተማ ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአሁኑ ሰዓት በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም