ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ ዓመታዊው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ዛሬ በኬንያ ክዋሌ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በውድድሩ መክፈቻ ቀን በተደረገው የግል የሰአት ሙከራ ውድድር ፅጌ ካህሳይ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። 

በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ ብስክሌተኛ ራሄል ግምባቶ ደግሞ አራተኛ ሆና አጠናቃለች።
 
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የሻምፒዮናውን የሜዳሊያ ሰንጠረዥ መምራት ጀምራለች።


 

ፅጌ ካህሳይ እ.አ.አ በ2024 በተካሄደው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና በግል ሰአት ሙከራ የነሐስ ሜዳሊያ ስታገኝ  በጎዳና ውድድር 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለከታል። 

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ29 ሀገራት የተወጣጡ ብስክሌተኞች በውድድሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል። 

ሻምፒዮናው እስከ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም