አዲስ አበባ ከተማ እና ኳላ ላምፑር ከተማ የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ ከተማ እና ኳላ ላምፑር ከተማ የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 10 /2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በማሌዥያዋ ኳላ ላምፑር ከተማ መካከል የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
የመግባቢያ ሰነዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) እና የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በተገኙበት መፈረሙን ከንቲባ አዳነኝ አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።