በክልሉ የአመራሩን አቅም በማጎልበት ልማታዊ እመርታዎችን የማስቀጠል ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የአመራሩን አቅም በማጎልበት ልማታዊ እመርታዎችን የማስቀጠል ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል
ጋምቤላ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማጎልበት እየተመዘገቡ ያሉ ልማታዊ እመርታዎችን የማስቀጠል ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
’’በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እመርታ’’ በሚል መሪ ሃሳበ በጋምቤላ ክልል ሁለተኛው ዙር የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።
በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን በዚሁ ወቅት፤ እንደ ሀገር እተመዘገቡ የሚገኙ የልማት እመርታዎችን ማፋጠን ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በክልሉ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችና ትሩፋቶችን ይበልጥ በማፍጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመረሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም የማጎልበቱ ተግባር ተጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመደመር መንግሥት በግብርና፣ በገጠር ትራንስፎረሜሽን፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በከተሞች ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች የታለመውን ሀገራዊ ለውጥ በተመሳሳይ ደረጃ ለመፈጸም የአመራሩን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የመገንባቱ ሂደትም እንዲሁ።
ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሕዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚቆይ ተመልክቷል።