ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሰርካዲስ ጉታ በ15ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች። 

በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ በስድስት ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በዘጠኝ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረገ የሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቦሌ ክፍለ ከተማ መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም