የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፦የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚያደርጉት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ብለዋል።