የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 11ኛውን የከተሞች ፎረም እንዲያስተናግድ ተመረጠ - ኢዜአ አማርኛ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 11ኛውን የከተሞች ፎረም እንዲያስተናግድ ተመረጠ
አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 11ኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም እንዲያስተናግድ ተመርጧል።
10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም "የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት" በሚል መሪ ቃል በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ሲካሄድ ቆይቷል።
በዛሬው እለትም የፎረሙ የማጠቃለያ መርሀግብር ተካሂዷል።
በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
በመርሀ ግብሩ በፎረሙ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከተሞች እውቅና ተሰጥቷል።
እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 11ኛውን የከተሞች ፎረም እንዲያስተናግድ ተመርጧል።